አማርኛ

በ 6 ለመገኘት ምቹ በሆኑ የማኅበረሰብ ጤና እንክብካቤ መስጫ ማእከላት ለእርስዎ መደበኛ፣ ድንገተኛ እና ሥር ሰደድ የሕክምና ፍላጎቶች ዋጋው ተመጣጣኝ እና ጥራቱን የጠበቀ የጤና እንክብካቤ እንሰጥዎታለን።

እርስዎ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚመጡ ታካሚ ሆኑ ለበርካታ ዓምታት ሲታከሙ የቆዩ ታካሚ ጥሩ አቀባበል እንደተደረገልዎት ሆኖ እንዲሰማዎት ማድረግ እና ሊሰጥ የሚችለውን ምርጥ የጤና እንክብካቤ ለእርስዎ መስጠት ዋንኛ ተልዕኮዋችን ነው። ይህን የምናሳከበት አንዱ መንገድ ባለሙያነቱ የተረጋገጠለት የቤት ሕክምና ሰጪ በመሆን ነው። ይህ ማለት ለእርስዎ ጤናዎን በተመለከተ በሚሰጧቸው ውሳኔዎች ላይ በእርስዎ የሕይወት ዘመን በሙሉ የተቀናጀ እንክብካቤ እና ድጋፍ እንሰጣለን ማለት ነው። ከእርስዎ እና ከቤተሰብዎ ጋር አጋርነትን በመፍጠር እንዲሁም በልዩ ደረጃ ከሰለጠኑ የሕክምና ባለሙያዎች፣ የአካባቢ ሆስፒታሎች፣ እና የማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመተባበር እኛ ለእርስዎ የሕክምና እንክብካቤ ከቤትዎ ጀምሮ እንክብካቤ የምንሰጥ መነሻዎ ነን።

የቋንቋ ችሎታዎች

አብዛኛዎቹ የእኛ ሠራተኞች በስፓኒሽኛ እና በሌላ ቋንቋዎች ሁለት ቋንቋዎችን አቀላጥፈው መናገር የሚችሉ ናቸው። ቁጥራቸው ከ200 በሚበልጡ ቋንቋዎች ታካሚዎች የእኛን ሠራተኞች ሊያናግሩዋቸው በሚፈልጉት ቋንቋ የሚያስተረጉሙ የስልክ አስተርጓሚዎች አሉን።

የእኛ ዶክተሮች

የእኛ የሕክምና ቡድን አባላት በቦርድ የብቃት ማረጋገጫ የተሰጣቸው የሕክምና ዶክተሮች፣ የጥርስ ሐኪሞች፣ የሥነ አእምሮ ሐኪሞች፣ ነርሶች፣ የሐኪም ረዳቶች፣ አዋላጆች እና ማኅበራዊ አገልግሎት ሠራተኞችን ያካተተ ነው።

አገልግሎቶች

 • የዓዋቂ ሰው ተቀዳሚ የሕክምና ክትትል
 • የአእምሮ ጤና ሕክምና ክትትል
 • የጥርስ ሕክምና ክትትል
 • የሴቶች ጤና እና ነፍሰጡርነት
 • ጨቅላ ሕፃናት እና ልጆች
 • የተማሪ ጤና
 • የሥነ አመጋገብ ትምህርት እና የክብደት ቁጥጥር

መገኛ አካባቢዎች

HHC-Albany Park / 3737 W. Lawrence Avenue, Chicago, IL 60625
(773) 751-7800


HHC-Lakeview Pediatric Center / 3048 N. Wilton Ave, 2nd Floor, Chicago, IL 60657
(773) 296-7580


HHC-Touhy / 2200 W. Touhy Ave., Chicago, IL 60645
(773) 751-1875


HHC-Devon / 1300 W. Devon Ave., Chicago, IL 60660
(773) 751-7850


HHC-Lincoln Square / 2645 W. Lawrence Ave., Chicago, IL 60625
(773) 275-1680


HHC-Wilson / 845 W. Wilson Ave., Chicago, IL 60640
(773) 506-4283


ለመጀመሪያ በሐኪም ለመታየት ሲመጡ ምን ይዘው መምጣት ያስፈልግዎታል

 • የእርስዎ ፎቶ ያለበት መታወቂያ ወረቀት
 • ወቅታዊ የመኖሪያ አድራሻ ማረጋገጫ
 • ወቅታዊ የስልክ ቁጥር
 • የሕክምና ካርድ ወይም የኢንሹራንስ ካርድ፣ ከሁለቱ አንዱ ካልዎት
 • ሁሉም እየወሰዱ ያሉዋቸው መድኃኒቶች ወይም ስም እና የመድኃኒት አወሳሰድን የያዘ ዝርዝር።
 • ተማሪ ከሆኑ ወይም በሕፃናት ሐኪም የሚታዩ ከሆነ የክትባት ሪኮርዶች።
 • አራስ ሕፃን የሚያመጡ ከሆነ ከሆስፒታል የተሰጡዎት የመውጫ ቅጾች።
 • ዕድሜያቸው ከ 18 በታች የሆኑ ልጆች ከወላጅ ጋር መምጣት አለባቸው።
 • ከጎን ለጎን ለሚታሰቡ ክፍያዎች [sliding scale fees] ብቁ መሆን እንዲችሉ ለመጨረሻ ጊዜ ክፍያ የተፈጸመበት ሰነድ ለገቢ ማረጋገጫ።

የልዩ ሕክምና መላኮች [Referrals] እና የሆስፒታል አጋሮች መላኪያ

አንዳንድ ጊዜ እኛ የማንሰጠውን የልዩ ሕክምና ክትትል ማግኘት የሚያስፈልግዎት ከሆነ ከእኛ አገልግሎቶች ውጪ ሊላኩ [ሪፌር ሊደረጉ] ይችላሉ። በልዩ ደረጃ የሰጠለነ የሕክምና ባለሙያ እንዲያገኙ አብረንዎት እንሠራለን። በተጨማሪ እርስዎ በ Heartland Health Centers ከሚያገኙት የሕክምና ክትትል ዕቅድ አንድ አካል መሆኑን ለማረጋገጥ ከልዩ ባለሙያ ሐኪሙ ጋር በቅርበት እንሠራለን።

በሆስፒታል ታኝቶ መታከም ካስፈለግዎት የተለያዩ የሆስፒታል አጋሮች በተጨማሪ አሉን።  የእኛ ዋንኛ አጋሮቻችን የሚከተሉት ናቸው፦ Advocate Illinois Masonic Medical Center፣ Swedish Covenant Hospital፣ Louis A. Weiss Memorial Hospital፣ Presence St. Francis Hospital፣ John H. Stroger Hospital of Cook County፣ እና Ann and Robert H. Lurie Children’s Hospital of Chicago።

የመድኃኒት ዋጋ ቅናሾች

የእርስዎ መድኃኒት ዋጋው ተመጣጣኝ እንዲሆን ለማድረግ ስንል በመድኃኒት ዋጋዎች ላይ የዋጋ ቅናሽ እንሰጣለን። 340 B ፕሮግራም በሚባለው አማካኝነት ማናቸውም ኢንሹራንስ የሌለው ታካሚ በጣም በዝቅተኛ ዋጋ መድኃኒቶችን ማግኘት ይችላል። እርስዎ Medicaid ወይም Medicare ካልዎት እና እርስዎ የሚያስፈልግዎት መድኃኒት በ Medicaid ወይም Medicare የማይሸፈን ከሆነ እርስዎ በተጨማሪ ይህን የዋጋ ቅናሽ ማግኘት ይችላሉ።

የ Heartland Health Center ታካሚዎች ሊሄዱባቸው እና የመድኃኒት ዋጋ ቅናሽ ሊያገኙ የሚችሉባቸው አራት የመድኃኒት መሸጫ መደብሮች አሉ። የእኛ ሦስት አጋሮቻችን የሆኑ መድኃኒት መደብሮች Pharmacy One በ Albany Park የሚገኝ፣ Morse L Pharmacy በ Rogers Park የሚገኝ እና Lawrence House በ Uptown የሚገኝ ናቸው። በእነዚህ የመድኃኒት መሸጫ መደብሮች አብዛኛዎቹ መድኃኒቶች ከ $10 ወጪ ይጠይቅዎታል። ይህ የመድኃኒቱን እና የማስወገጃ ወጪውን ያካትታል። በተጨማሪ ከ Walgreens ጋር በአጋርነት እንሠራለን። በ Walgreens አብዛኛዎቹ መድኃኒቶች ከ $16 ወጪ ይጠይቅዎታል። የእነርሱ የማስወገጃ ወጪ ከፍተኛ ስለሆነ የሚጠይቁት ዋጋ ትንሽ ከፍ ያለ ነው።

ተቀባይነት ያላቸው ክፍያዎች እና መክፈያ ዘዴዎች

ማን ስንት ገቢ እንዳለው ከግምት ሳይገባ የእኛ አገልግሎቶች ለሁሉም ሰው ተደራሽ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ኢንሹራንስ ለሌላቸው ታካሚዎች የጎን ለጎን ክፍያ [sliding fee scale] አገልግሎትን እሰጣለን። ለዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ታካሚዎች አንዴ በሐኪም ለመታየት የሚከፈለው መጠኑ $35 የሆነው የጎን ለጎን ክፍያው ሁሉንም የላብራቶሪ እና እንደ የደረት እና የአጥንቶች ራጂዎችን ያካትታል። ስለ የሚጠየቁት ክፍያ ጥያቄ ካልዎት የእኛን የክፍያ መጠየቂያ መመሪያ በስልክ ቁጥር (773) 296-7544 ያነጋግሩ።

Medicaid፣ Medicare፣ የግል የጤና ኢንሹራንስ እንቀበላለን እና ኢንሹራንስ ለሌላቸው ሰዎች ዋጋቸው ተመጣጣኝ የሆኑ አገልግሎቶችን እሰጣለን።

የጤና ኢንሹራንስ ይፈልጋሉ

ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ የሕክምና ክትትል የመስጠት ግዴታ ሕግ [Affordable Care Act (ACA)] እንዲሁም በተጨማሪ Obamacare በመባል የሚታወቀው አብዛኛዎቹ ሕጋዊ የአሜሪካ ነዋሪዎች ዝቅተኛ የመሠረታዊ አስፈላጊ የጤና ክትትል የመድን ሽፋን እንዲኖራቸው ወይም በዓመቱ ሙሉ ወይም በከፊል የጤና ኢንሹራንስ ከሌላቸው የኃላፊነት መጋራት ክፍያ (ቅጣት) እንዲከፍሉ መብት ይሰጣቸዋል።

የጤና ኢንሹራንስ በ Medicaid፣ Medicare፣ የግል ኢንሹራንስ፣ በአሠሪ የሚሸፈን ኢንሹራንስ፣ ወይም በ ACA Marketplace በኩል ማግኘት ይቻላል። ከእነዚህ የመድን ሽፋን ዓይነቶች አንዱ አስቀድሞ ያልዎት ከሆነ ሌላ እንዲኖርዎት አያስፈልግዎትም። አንዳንድ ግለሰቦች የ ACA መብት የላቸውም። ለምሳሌ፦ ሰነድ አልባ ግለሰቦች እና በ Deferred Action for Childhood Arrivals (DACA) ሥር ያሉ እና የቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባዎች የጤና መድን ሽፋን እንዲኖራቸው አይገደዱም። የገቢ ግብር ሰነዳቸውን ፋይል በሚያደርጉበት ጊዜ የኃላፊነት መጋራት ክፍያን እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ። ሆኖም ግን የገቢ ግብር ሰነዳቸውን ፋይል በሚያደርጉበት ጊዜ ይለፈኝ ብለው መጠየቅ ይችላሉ። በይለፈኝ ጉዳይ ስለመታየት በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ የእኛን ሆትላይን [ነጻ የስልክ መስመር] መደወል ይችላሉ።

የእኛ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው የማመልከቻ አማካሪዎች የእርስዎን የመድን ሽፋን እኛ የምንቀበለው ስለመሆኑ ሊያሳውቅዎት፣ የእርስዎን ብቁነት ሊወስኑ እና ለመድን ሽፋን በሚያመለክቱበት ጊዜ እገዛ ሊሰጥዎት ይችላሉ። በሚከተሉት ቀናት እና የሥራ ሰዓታት ፊት ለፊት የሚሰጥ እገዛ አገልግሎት አለን፦

 • በየሳምንቱ ሰኞ እና ረቡዕ፦ ከጠዋቱ 10 am እስከ ቀኑ 4 pm በ HHC-Wilson, 845 W. Wilson
 • በየሳምንቱ ማክሰኞ እና ሐሙስ፦ ከጠዋቱ 10 am እስከ ቀኑ 4 pm በ HHC-Devon, 1300 W. Devon
 • በየሳምንቱ ረቡዕ፦ ከቀኑ 12 pm እስከ ቀኑ 4 pm በ HHC-Lincoln Square, 2645 W. Lawrence
 • የሳምንቱ ዓርብ፦ ከጠዋቱ 9 am እስከ ቀኑ 12 pm በ HHC-Albany Park, 3737 W. Lawrence
 • ወይም ወደ የእኛ ሆትላይን [ነጻ የስልክ መስመር] (773) 751-7062 መደወል ይችላሉ።

ስለ Heartland Health Centers ተጨማሪ መረጃ

Heartland Health Centers የማኅበረሰብ፣ በትምህርት ቤት የተቋቋሙ፣ የልዩ ሕክምና መስጫ ማእከላትን ጨምሮ በ15 መገኛ አካባቢዎች የሚንቀሳቀስ በፌደራል ደረጃ የሙያ ብቃቱ የተረጋገጠለት የጤና እንክብካቤ መስጫ ማእከል ነው። የቺካጎን ሰሜናዊ ክንፍ እና በአቅራቢያው ያሉ የከተማ ደጃፍ ሠፈሮችን የምናገለግል ስንሆን በ2015 ዓ.ም. ለ 19,000 ታካሚዎች የሕክምና አገልግሎት ሰጥተናል። እንደ የሙያ ብቃቱ የተረጋገጠለት እስከ ቤት የሚደርስ የሕክምና እንክብካቤ ሰጪነታችን ዋጋው ተመጣጣኝ እና አጠቃላይ ተቀዳሚ የሕክምና ክትትል፣ የአፍ ጤና፣ የሥነ አእምሮ ጤና ክትትል አገልግሎቶችን እንሰጣለን። በ The Joint Commission ስለተቀዳሚ የቤት ሕክምና ክትትል ሰጪነት [Primary Care Medical Home] ዕውቅና አለን። ፌደራል የጥራት ደረጃ መቆጣጠሪያ ምዘና በ2014 ዓ.ም. በቺካጎ ከሚገኙ በፌደራል የብቃት ማረጋገጫ ከተሰጣቸው የጤና ማእከላት አንዱ እንደሆንን አድርጎ ደረጃ ሰጥቶናል።

FQHC ምንድን ነው?

Federally Qualified Health Center (FQHC) በቂ አገልግሎት ለማይደረሳቸው አካባቢዎች እና ሕዝቦች የጤና እንክባካቤን ይሰጣል፣ የጎን ለጎን የሕክምና ክፍያ ወጪ መሸፈን ዘዴን ይሰጣል፤ አጠቃላይ አገልግሎቶችን ያቀርባል፣ ቀጣይ የሆነ የጥራት ማረጋገጫ ፕሮግራም አለው እና አብዛኛዎቹ ታካሚዎች የሆኑ የሚገኙበት የቦርድ አባላት መካከል በተመረጡ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሥራውን ያከናውናል። በአገር አቀፍ ደረጃ ከ 18 ሚሊዮን በላይ ታካሚዎችን የሚያገለግለው FQHC የፌደራል የገንዘብ ርዳታ እና ከ Medicare እና Medicaid የተሻሻለ የተመላሽ ገንዘብ አደራረግ ድጋፍ ይደረግለታል።